ይህ አፕሊኬሽን ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን ባህላዊ መድሃኒቶች እና ተክሎች ከብዙ በጥቂቱ ይዘረዝራል። በተጨማሪም ባህላዊ መድሃኒቶች ላይ የተደረጉትን ሳይንሳዊ ምርምሮች ከብዙ በጥቂቱ ይዘረዝራል ። ከእነዚህ በተጨማሪም "በሰው ላይ በሽታን ስለሚያመጡ ጎጂ ተዋህሲያን" ፣ "ስለ መድሃኒት አይነቶች እና ጥቅማቸው" ይዘረዝራል ። ይህን አፕሊኬሽን ለመጀመሪያ ግዜ ሲከፍቱ ጥሩ ኢንተርኔት ኮኔክሽን ያስፈልጋል ። የምስሎቹን ምእራፎች ስትከፍቱ በትክክል ዳውንሎድ እንዲሆኑ በጣም ጥሩ ኢንተርኔት ኮኔክሽን ያስፈልጋል ። የመወያያ ገፁን ለመጠቀም የኢንተርኔት ኮኔክሽን ያስፈልጋል ። የመወያያ ገፁን ለመጀመሪያ ግዜ ሲከፍቱ ስለራሶ የተወሰኑ መረጃዎችን መሙላት ያስፈልጋል ። ይህ ፅሁፍ የተዘጋጀው ከተለያዩ ሳይንሳዊ ጥናቶች ፅሁፍ ውስጥ ነው ። አፕሊኬሽኑን ያለ ኢንተርኔት ኮኔክሽን መጠቀም ይቻላል ። አፕሊኬሽኑ ከ 300 ገፅ በላይ መረጃዎችን ይዟል ። ኢትዮጵያ ለብዙ በሽታዎች መድሃኒት የሚሆኑ ተክሎችን የታደለች ሃገር ነች ። ከ 70% በላይ የሆነው ያገሬ ገበሬ እነዚህን ተክሎች ለመድሃኒትነት በብዛት ይጠቀማል ።
ሳይንሳዊ እና ውጤታማ በሆነ መልኩ ይህንን ፀጋ መጠቀም ይኖርብናል ።
መልካም ንባብ ይሁንላችሁ ።