የሕይወትን ፍለጋ ቡድን አራቱን ጉዞዎች፣ ማለትም ማመን፣ ማደግ፣ መኖርና
መለወጥ የተሰኙትን ጉዞዎች በጋራ ለመጓዝ የወሰኑ ወጣቶች የሚመሠርቱት
ቡድን ነው። በራሳችሁ እነዚህን አራት ጉዞዎች መጓዝ ግሩም ነው፤ ነገር ግን
ሌሎች አብረዋችሁ ይህንን ጉዞ ለማድረግ ፍቃደኞች ከሆኑ ሰዎች ጋር ይህንን
ጉዞ ማድረግ የበለጠ ደስ የሚልና ሕይወትን የሚለውጥ ነው። ቡድኑ ለ 40
ሳምንታት የሚቆይ ነው። አንዳንድ የእረፍት ሳምንታትን ከጨመራችሁበት
ደግሞ ሁሉንም ነገር ለማጠናቀቅ አንድ ዓመት ይፈጃል። ጉዞውን ስትጨርሱ
በእምነታችሁ ይበልጥ ጠንካሮች፣ በሕይወታችሁ እያደጋችሁ ያላችሁና ቀስ
በቀስ በየጊዜው ይበልጥ ክርስቶስን የምትመስሉ ትሆናላችሁ። ለሕይወት
ዘመናችሁ ጓደኛ የሚሆኑ ሰዎችም ታገኙበት ይሆናል። የራሳችሁን ቡድን
ለመጀመርም ትወስኑ ይሆናል! ይህንን የእሳት ብልጭታ ንኩትና እግዚአብሔር
ልባችሁን በራሱ ልብ እንዲያቀጣጥለው ፍቀዱለት! ይህንን የፍቅር አብዮት
ተቀላቀሉት!
Reach4Life Bible (Amharic) facilitates change through bringing young people to Christ, discipling them, and teaching them Bible-based life skills addressing issues specific to teens and young adults ages 12 to 25. The devotional focuses on the 4 journeys: how to be saved, growing in Christ, how to face challenges, and how to be a change agent yourself. Additionally, the Reach4Life program implements an effective teaching and discipling method called peer education. Peer influence can be such a strong factor in a youth’s decision-making process, that when youth are transformed by the Word of God and choose to lead their peers we consistently see dramatic improvements in behavior and life choices.